Terbinos Logo

ከተጓዦች የሚጠበቁ ሁኔታዎች፡

  • አርምሞ መጠብቅ ወይም ለፀጥታ እና ለፀሎት ልዩ ትኩረት ማድረግ
  • መንፈሳዊ ጉዞ እና ፀበል ስለምንሔድ ለስጋዊ ምቾት ብዙም ትኩረት አለመድረግ
  • የስልክ ኔትዎርክ በአካባቢው ስለሌለ ዘመናዊ ስልኮችን አለመያዝ
  • ለመኝታ የሚሆን ምንጣፍ፣ ለፀበል መጠመቂያ አዲስ ቁምጣ፣ የፀበል መቅጃ ጀሪካን እና ኩባያ መያዝ
  • ምግብ ቤቶች ስላሉ ለምግብ ብዙም አለመጨነቅ፣ በተጨማሪም በሶ፣ ቆሎ እና ሌሎች የግል መገልገያ የሆኑ መያዝ
  • ፀበል በሚጠጣበት ወቅት ራቅ ብሎ ወደ ወንዝ አካባቢ እና ጥላ ስር መጠጣት
  • አካባቢው ሞቃታማ በመሆኑ ስስ ልብሶችን እና ለሳምንት የሚበቃንን ብቻ መያዝ

ህግና ደንቦች፡

  • ምዕመናንና ምዕመናት ንስሃ መግባት አለባቸው፣ ንስሃ ሳይገቡ ወደ ፀበሉ መግባት የተከለከለ ነው!
  • ጫማ አውልቁ የሚል ምልክት ካለበት ጀምሮ ጫማ ማውለቅ አለብን!
  • አዲስ ተመዝጋቢ ከሆንን መታወቂያ/ፓስፖርት መያዝ አለብን!
  • ገድል በሚነበብበት ቦታ እና ፀበል በሚጠመቅበት ቦታ ማውራት የተከለከለ ነው!
  • ለሴቶች ጥፍር ለወንዶች ፀጉር ማሳደግ የተከለከለ ነው!
  • ሴቶች በልማደ አንስት (የወር አበባ) ወቅት ከ8 ቀን በኋላ ነው ወደ ፀበሉ መግባት የሚቻለው!
  • ህልመ ሌሊት የታየው ሰው ከ24 ሰዓት በኋላ ገላውን ታጥቦ ወደ ፀበሉ መግባት ይችላል!

About Us /ስለ እኛ/

ስለ እኛ

ተርቢኖስ የጉዞ ማህበር(አስጎብኝ) እና የጉዞ ወኪል አገልግሎት በ2016 ዓ/ም ለበጎ አላማ የተመሰረተ መንፈሳዊ ማህበር ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አድማሱን እና ተደራሽነቱን እያሰፋ ይገኛል። በስሩ በርካታ ሰራተኞች እና የክብር አባላት ያሉት ሲሆን በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገራት ቢሮችን በመክፈት እየሰራን እንገኛለን፡፡ ድርጅታችን በተለያዩ የሶሻል ሚዲያ አማራጮች የሚገኝ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ዩቱዩብ፣ ቲክቶክ፣ ሊንክድኢን እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በክብር አባልነት ቋንቋየነሽ ሚድያ እና መምህር ተስፋዬ አበራ ዩቱዩብ ቻናል አብረውን ይሰራሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከ25 በላይ ሠራተኞች ሲኖሩት ማህበሩ በክብር አባላቶቹ በኩል በአውሮፓ እና አሜሪካ ቅርንጫፉን በመክፈት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በዋናነት ከአውሮፓ እና አሜሪካ የሚመጡ መንፈሳዊ ተጓዞችን በመቀበል በርሜል ቅዱስ ጊዮርጊስ ፀበል እያጓጓዘ ይገኛል። በዚሁ አጋጣሚ በቀጣይ 2018 ዓ/ም ወደ ቅድስት ሀገር እየሩሳሌም መንፈሳዊ ጉዞ የምንጀምር መሆኑን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው፡፡

About Us

- Turbinos Travel Association (tour operator) and travel agency service founded in 2024 for a good cause It is an association and has been expanding its scope and reach lately. A large number of employees and honorees We have members and we are working on opening offices at home and abroad. Our organization is in a variety of Social media options are available, of which are YouTube, TikTok, LinkedIn and so on. We are also working with the Department of Health and Human Services and the Department of Health and Human Services.

In addition, it has more than 25 employees, and the association operates its branch in Europe and the United States through its honorary members. It operates openly, welcoming spiritual pilgrims mainly from Europe and the United States St. George's Cemetery is under construction. In 2018, the Holy Land of Jerusalem It is with great joy that we announce that we are embarking on a spiritual journey.

Services/የምንሰጣቸው አገልግሎቶች/

We cover anything that is needed for your digital presence.

Contact Us

Addis Ababa
መገናኛ ገነት ኮሜርሻል ሴንተር 4 ኛ ፎቅ 403
ቁ/2 ቦሌ 22 ፌስቲቫል ህንፃ 6ኛ ፎቅ 603
+251-9-1010-1073
+251-9-1818-1867
+251-9-6842-4344
+251-9-6942-4344
+251-9-7042-4344
Washington DC
በቅርብ ቀን
+120-6556-8244
Germany
+491-7-6417-50635
+491-7-6417-51202